ስለ እኛ

"ሐዊር" የግዕዝ ቃል ሲሆን "ጉዞ" የሚል ትርጉም አለው። ሐዊር በዋናነት የመንፈሳዊ ጉዞ መረጃን በአንድ ቋት በመሰብሰብ ምዕመናኑ በቀላሉ መረጃ እንዲያገኙ የሚያደርግ በመሆኑ ይሄንን ስያሜ ያገኘ ሲሆን የመንፈሳዊ ጉዞ መረጃዎችን፣ የቅዱሳን መካናት(ገዳማትና አድባራት) ታሪክ፣ የቅዱሳንን ታሪክ፣ የንግስ በዓል መረጃዎችን በመላው ዓለም ላሉት ምዕመናን የሚያደርስ ስርዓት(platform) ነው። ሐዊር፡ የጉዞ አዘጋጆች የእጅ ስልካቸውን ተጠቅመው የጉዞ መረጃቸውን በቀላሉ ለምዕመናን የሚያደርሱበት "ሐዊር-ጉዞ አዘጋጅ" የተሰኘ መተግበሪያም አለው።

ሐዊር ይሄንን የጉዞ መተግበሪያ ሀሳብ ይዞ ሲነሳ ምዕመናንና ምዕመናት እንደየፍላጎታቸው በሚፈልጉበት ጊዜ ወደሚፈልጉበት ገዳማትና አድባራት ሂደው እንዲባረኩ፣ እንዲጽናኑ፣ እንዲረዱና ታርካቸውን እንዲያውቁ ማድረግ ሲሆን በዋናናት ከታች የተዘረዘሩትን አላማዎችን በመያዝ ነው፡፡

1. የቤተክርስቲያንን የገዳማትና አድባራት ሙሉ ታርክ ማለትም በቦታው የሚከብር ቅዱስ፣ የቦታው ቃልኪዳን፣ በቦታው የሚከበሩ ቅዱሳን ታርክ፤ የገዳሙ/አድባሩ/ን የምሥረታ ታርክ፣ የሚገኝበት ክልል፣ ዞን፣ ሀገረ ስበብከት…. በመያዝ የቤተክርስቲያንን መረጃ ማቆየት፡፡

2. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክንን በዓለም አቀፍ ማህረ ሰብ ማሳወቅና እንዲትጎበኝ ማድረግ፡፡

3. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ገዳማትና አድባራት የተደራጀ መረጃ እንዲነራት ማድረግና መረጃውን አደራጅቶ ማስቀመጥ፡፡

4. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ገዳማትና አድባራት ከምእመናንና ከሚጎበኟት አካላት ትኩረትና ድጋፍ እንድታገኝ ማድረግ

5. ምዕመናን በቤታቸው ተቀምጦ መሄድ የሚፈልጉበትን ገዳምና አድባር መርጦ መቼና ማን እንዳዘጋጀ፣ በምናይል ዋጋ እንደተዘጋጀ፣ ለስንት ቀን እንደተዘጋጀ አውቀው ክፍያ ከፍሎ ወንበር አስይዞ ለመጓዝ ብቻ እንዲሄዱ ማድረግ፡፡

6. ቤተክርስቲያን ሥርዓቷ ሳይበረዝ ጊዜውን በዋጀ መልኩ እንዲትጠቀም ማድረግ፡፡

7. ወደ ገዳማትና አድባራት ጉዞ የሚያዘጋጁ አካላት ትክክለኛ የቤተክርስቲያን ልጆችና መረጃ ያላቸው ብቻ ማድረግና በጉዞ ስም የሚነግዱና የሚያጭበረብሩ አካላት እንዳይኖሩ ማድረግ፡፡

8. ጉዞ አዘጋጅ አካላት ብዙ ሳይደክሙና ብዙ ወጪ ሳያወጡ የሚያዘጋጁትን ጉዞ በማደራጀት እንዲሰራር ማድረግ፡፡

9. የተያዙ ምዕመናንን በሚፈልጉበት ወቅት በተዘጋጀ ገዳማትና አድባራት መስኮት ማላቀቅና መገኘት